ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የዒድ ሰላት በስኬት እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላትን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የዒድ ሰላት በስኬት እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት 1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የዒድ ሰላት በከተማችን ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል ብለዋል።


 

መርሐ ግብሩ በስኬት እንዲከናወን ያደረጋችሁ የሃይማኖት አባቶችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ ህዝበ ሙስሊሙንና አጠቃላይ የከተማችን ነዋሪዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የዒድ አልፈጥር በዓል እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም