በፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከቦርንማውዝ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከቦርንማውዝ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል።
ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ቦርንማውዝ ከማንችስተር ዩናይትድ በቫይታሊቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቦርንማውዝ በ41 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ዩናይትድ በ54 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ባለሜዳው ቦርንማውዝ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። በጨዋታዎቹ ላይ አራት ጊዜ ሲያሸንፍ ስድስት ጊዜ አቻ ወጥቷል።
ቡድኑ ባለፉት አራት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል።
ተጋጣሚው ማንችስተር ዩናይትድ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ እየተመራ ጠንካራ ግስጋሴ እያደረገ ነው።
ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሶስቱን ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይቷል።
ቦርንማውዝ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ህልሙን ለማስቀጠል ይፋለማል።
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እየተፎካከረ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ነጥብ ማግኘት ወሳኝ ነው።
ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የ43 ዓመቱ ስቱዋርት አትዌል ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት እስከ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።