ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር ላይ ይሳተፋል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ባዘጋጀው የወዳጅነት ውድድር ላይ እንደሚሳተፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር የሚያካሂደው የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር በቱርክዬ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዝያ 10 ይከናወናል።

በዚህ ውድድር ላይ ከተለያዩ አህጉራት የተውጣጡ ሀገራት የሚሳተፉ ሲሆን፤ የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ጋር በፈጠረው ግንኙነት ከአፍሪካ ከሚሳተፉ ሁለት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆን ችላለች።


 

በዚህም ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተሳታፊ እንደሚሆን መረጋገጡን ፌዴሬሽኑ ጠቁሟል።

በዚህ ውድድር ላይ አስተናጋጇ ቱርክዬን ጨምሮ ኢትዮጵያ፣ ኖርዌይ፣ ኡዝቤኪስታን፣ ኮስታሪካ፣ ፓራጓይ፣ ዩራጓይ እና ሞሮኮ ይሳተፋሉሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም