በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 4 ነጥብ 48 ኪሎግራም የሚመዝን ኮኬይን ከነአዘዋዋሪው ተያዘ - ኢዜአ አማርኛ
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 4 ነጥብ 48 ኪሎግራም የሚመዝን ኮኬይን ከነአዘዋዋሪው ተያዘ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018(ኢዜአ) ፦ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 4 ነጥብ 48 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕጽ ሊያሳልፍ የሞከረ አንድ ናይጀሪያዊ ተጠርጣሪን መያዙን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገለጸ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መረጃ እንደገለፀው መነሻውን ናይጄሪያ ሌጎስ መዳረሻውን ህንድ ባደረገ ተጠርጣሪ ሻንጣ ውስጥ ተደብቆ ሊያልፍ የነበረ 4 ነጥብ 48 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ይዟል።
የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ሰራተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ አማካኝነት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
172 ፍሬ ብዛት ያለው 4 ነጥብ 48 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ አደገኛ ዕፅ በአለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በተገጠመ ዘመናዊ ኤክስሬይ መሣሪያ መለየቱንም አመልክቷል።
የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ እንደሚያመለክተው ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ተጠርጣሪውና ሌሎች መረጃዎች ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፈዋል።