መቻል በድል ጉዞው ቀጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል በድል ጉዞው ቀጥሏል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር መቻል ይርጋጨፌ ቡናን 4 ለ 1 ረቷል።
በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴናፍ ዋቁማ፣ መዲና አወል፣ ቱሪስት ለማ እና ትንቢተ ሳሙኤል የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቤተልሄም ፈርኦን ለይርጋጨፌ ቡና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የመቻሏ ጽዮን ፈየራ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ41 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸውን ጨዋታዎች ብዛት 12 አድርሷል።
በአንጻሩ በሊጉ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ይርጋጨፌ ቡና በ11 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት 11 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ሲዳማ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ 19ኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የ20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከመጋቢት 11 እስከ 13 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።