ድሬዳዋ ከተማ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ድሬዳዋ ከተማ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና ሸገር ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርታ ወልዴ በሰባተኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ ሸገር ከተማ መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ ህይወት አመንቴ በ54ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ጎል ለድሬዳዋ ከተማ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
የድሬዳዋ ከተማዋ መአዛ አብደላ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ20 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ሸገር ከተማ በ38 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ አልቻለም።
ዛሬ በተደረጉ የ19ኛ ሳምንት ሌሎች ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።