ቀጥታ፡

በቅርቡ የጸደቀው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ለብዝሃ ቱሪዝም ዕድገት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ በቅርቡ የጸደቀው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ለኪነ ጥበብ ቱሪዝም ትኩረት በመስጠት ለብዝሃ ቱሪዝም ዕድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው

በሰዓሊ ተገኔ ኩንቢ በጣሊያን ቬንስ በሚካሄደው 61ኛው የቬኒስ ቢየናሌ የኢትዮጵያን ፓቪሊዮን "የዝምታ ቅርጾች" የተሰኘ አውደ ርዕይ ዙሪያ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና የኤግዚቢሽኑ አዘጋጅ ሰዓሊ ተገኔ ቁንቢ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የምትሳተፍበት የቬኒስ ቢየናሌ በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊና ታዋቂ ዝግጅቶች አንዱ ነው።


 

በኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ ለብዝሃ ቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት በመስጠት አዳዲስና ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስፋፋት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚኖረውን አበርክቶ ማሳደግ የሚያስችል የቱሪዝም ፖሊሲ መፅደቁንም ገልጸዋል።

አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ብዝሃ ቱሪዝምን ለማሳደግ ታሪካዊና ባህላዊ የቱሪስት መስህቦችን፣ ኢኮ-ቱሪዝም፣ ጂኦ ቱሪዝም፣ የቡና ቱሪዝም፣ ኮንፍረንስ ቱሪዝም እና የአርት/የኪነ ጥበብ ቱሪዝም ዘርፎችን አካቷል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በጣሊያን ቬኒስ ከተማ በሚካሄው ዓለም አቀፍ ዝግጅት የኢትዮጵያ ፖቪሊዮን "የዝምታ ቅርጾች" በማዘጋጀት የኪነ ጥበብ ስራዎቿን የምታስተዋውቅበት መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

ይሄውም አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ለብዝሃ ቱሪዝም የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፤ ኤግዚቢሽኑ ዓለም አቀፍ የሥዕል ሥራዎችን ውድድር ያለፉ አርቲስቶች ቀርበው የሀገራቸውን ገፅታ የሚገነቡበትና የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው ብለዋል።

መድረኩ የኢትዮጵያን የኪነ ጥበብ ሥራዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚያስችል መሆኑን በማንሳት፤ የኢትዮጵያን ልዩ የሙዚቃ፣ ስዕልና ቴአትር ጥበብ እንደሚያሳይ ገልጸዋል።


 

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፤ ኢትዮጵያ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ባላት ዕምቅ አቅም ልክ ተጠቃሚ አልነበረችም ብለዋል።

ይሁን እንጂ ከለውጡ ወዲህ ባለው የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ኪነ ጥበብ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ሰዓሊ ተገኔ ቁንቢ ያዘጋጀው አውደ ርዕይ "ዝምታ" የኢትዮጵያን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያቀርብ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በስዕልና ቅርፃ ቅርፅ ዘርፍ ያሉ ሰዎች በስፋት እንዲሳተፉ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ስኬታማ ስራ ነውም ብለዋል።

አውደ ርዕዩ የኢትዮጵያ አመለካከትና ፈጠራ የተገለጠበት ድንቅ ዝግጅት መሆኑን ገልጸዋል።


 

"የዝምታ ቅርጾች" አውደ ርዕይ አዘጋጅ ሰዓሊ ተገኔ ቁንቢ፤ ዝምታ ባዶ ሳይሆን በውስጡ የታመቀ ሀሳብ ያለው ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም