ባህር ዳር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው መርሐ-ግብር ዓይናለም መኮንን በ45ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
የባህር ዳር ከተማዋ መንደሪን ታደሰ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ከአምስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ባህር ዳር ከተማ በ13 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በበኩሉ በ10 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
አርባምንጭ የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት 12 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።