በተጠባቂው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሃዋሳ ከተማ ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሃዋሳ ከተማ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሃዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ጨዋታው ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄዷል። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።
የሃዋሳ ከተማዋ ታሪኳ ጴጥሮስ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ50 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። የሊጉን መሪነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳግም የመረከብ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሳሳይ 50 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
ሃዋሳ ከተማ በ39 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።