ቀጥታ፡

የፊቼ ጫምባላላ እሴቶችን አጠናክረን እናስቀጥላለን - ወጣቶች

ሐዋሳ፤ መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፡- ከአባቶች የወረስነውን የፊቼ ጫምባላላ የሠላምና አብሮነት እሴቶች አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ የሲዳማ ክልል ወጣቶች ተናገሩ፡፡

የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሐዋሳ ሶሬሳ ጉዱማሌ በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል፡፡

ከኢዜአ ጋር ቆይታ የነበራቸው የበዓሉ ታዳሚ ወጣቶች በዚሁ ወቅት፤ ከአባቶቻችን የወረስነውን የፊቼ ጫምባላላ የሠላምና አብሮነት እሴት አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

በዓሉ ፍቅርና አብሮነት ጎልቶ የሚገለፅበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ሁሉም እኩል የሚታይበት ለእንስሳት ደግሞ ከወትሮው በተለየ መልኩ እንብካቤ የሚቸርበት ዕለት መሆኑን አስረድተዋል።


 

ወላጆቻችን ያስተላለፉልንን እኛም ጠብቀን ሳይበረዝ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የሚጠበቅብንን እንወጣለንም ብለዋል።

በዓሉ የተጣሉ የሚታረቁበትና ያለው ለሌለው በማካፈል በደስታ የሚያከብረው መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም