ቀጥታ፡

አትሌት ፎቴን ተስፋይ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገችው የማራቶን ውድድር  አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በባርሴሎና ማራቶን በሴቶች ውድድር አትሌት ፎቴን ተስፋይ አሸንፋለች።

አትሌት ፎቴን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ ፈጅቶባታል። 

በዚህም መሠረት የቦታውን ክብረወሰን በመስበር ያሸነፈች ሲሆን፤ በርቀቱ የዓለም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓትም አስመዝግባለች።


 

አትሌቷ በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ ድል ቀንቷታል።

በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዘይነባ ይመር ሶስተኛ፣ ጫልቱ ጭምዴሳ አራተኛ እና ያልጋነሽ እስከመች አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል ።

የባርሴሎና ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የነሐስ ደረጃ የተሰጠው የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም