ቀጥታ፡

ቦሌ ክፍለ ከተማ እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፍቅረአዲስ ገዛኸኝ በ34ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ጎል ቦሌ ክፍለ ከተማን መሪ አድርጓል።

ሔለን መሰለ በ62ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ጎል ለአዳማ ከተማ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።


 

የአዳማ ከተማዋ ነጻነት መና የጨዋታው ኮከብ ሆና መርጣለች።

ውጤቱን ተከትሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ በ31 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዛሬ አስቀድሞ በተካሄደ የ19ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ክፍለ ከተማን 5 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም