ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሊጉ መሪ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሊጉ መሪ ሆነ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ክፍለ ከተማን 5 ለ 0 ረትቷል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ እሙሽ ዳንኤል ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እፀገነት ግርማ፣ ንግሥት በቀለ እና ታሪኳ ደቤሶ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ሁለት ግቦችን ያስቆጠረችው እሙሽ ዳንኤል የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ 16ኛ ድሉን ያስመዘገበው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ50 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በጊዜያዊነት ተረክቧል።
በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በ15 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።