ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዌስትሃም ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በርናንዶ ሲልቫ በ31ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ማንችስተር ሲቲ መሪ ሆኗል።
ኮንስታንቲኖስ ማቭሮፓኖስ በ35ኛው ደቂቃ የዌስትሃምን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ብልጫ ቢወስድም ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ አንድ ተስተካካይ የሚቀረው ማንችስተር ሲቲ በ61 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ዘጠኝ ከፍ ብሏል።
ውሃ ሰማያዊዎቹ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ የዋንጫ የማንሳት እድላቸው የጠበበ ሆኗል።
ዌስትሃም ዩናይትድ በ30 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 17ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ወሳኝ አንድ ነጥብ አግኝቷል።
ዌስትሃም ከሶስት ወራት በኋላ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
የሊጉ መሪ አርሰናል ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።