አርሰናል ኤቨርተንን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ኤቨርተንን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት አርሰናል ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ዮኮሬስ በ89ኛው እና ማክስ ዶውማን በ97ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ 21ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ70 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 10 ከፍ አድርጓል።
መድፈኞቹ በተፈተኑበት ጨዋታ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝተዋል።
ተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በለንደን ስታዲየም ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ቼልሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
አንቶኒ ጎርደን የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።