ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ብራይተን ድል ሲቀናው በርንሌይ እና ቦርንማውዝ አቻ ተለያይተዋል 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5 /2018(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ማምሻውን ተጀምሯል።

በስታዲየም ኦፍ ላይት በተደረገው ጨዋታ ብራይተን ሰንደርላንድን 1 ለ 0 ተሸንፏል።

ያንኩባ ሚንቴ በ58ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

የሰንደርላንዱ ክሪስ ሪግ በ50ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል በቪዳዮ በታገዛ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ተሽሯል።

በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ብራይተን በ40 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሰንደርላንድ በተመሳሳይ 40 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

በተርፍሙር ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ በርንሌይ እና ቦርንማውዝ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። 

ውጤቱን ተከትሎ በርንሌይ በ20 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ቦርንማውዝ በ41 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 የሊጉ መሪ አርሰናል ከኤቨርተን፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ምሽት አምስት ላይ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም