ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለፊቼ ጨምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ ማንነት መገለጫ፣ የኢትዮጵያችን ደግሞ አንዱ ውብ ቀለም ነው ብለዋል።

በዓሉ የሰላምና የዕርቅ ዋዜማ፣ የፍቅርና የአንድነት ማሳያ መሆኑን ገልጸው ያለፈውን በይቅርታ ትተን፣ አዲሱን ዘመን በአዲስ ተስፋና በታላቅ ራዕይ ለመቀበል ሁላችንም በአንድነት የምንቆምበት ወቅት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘመኑ የሰላም፣ የጤናና የብልጽግና እንዲሆንም ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም