ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድል ቀንቷቸዋል 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ወገኔ ገዛኸኝ እና አማኑኤል ኤርቦ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ከሁለት የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ መድን በ28 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ19 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።


 

በሌላኛው መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዊት ገብሩ በ10ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የድሬዳዋ ከተማው ተከላካይ ሲያም ሱልጣን በ84ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ28 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 13ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።

በአንጻሩ በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በተመሳሳይ 28 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም