ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባና ሌሎች ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በስፍራው በመገኘት ሃዘናቸውን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባና ሌሎች ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በስፍራው በመገኘት ሃዘናቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባና ሌሎች ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በስፍራው በመገኘት ሃዘናቸውን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸዋል።
መንግሥት ለአደጋው ተጎጂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን እንዳለበት ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰትም አስፈላጊው የጥንቃቄ ተግባራት ሊከናወኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።