ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ተመልሰው በቀጥታ ወደ አርባምንጭ አቀኑ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ተመልሰው በቀጥታ ወደ አርባምንጭ አቀኑ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ተመልሰው በቀጥታ ወደ አርባምንጭ ማቅናታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በአርባ ምንጭ ዙሪያ እና በመላው ጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሐዘናቸውን ለመግለጽ እና የሚከናወኑ የድጋፍ ስራዎችን እንደሚገመግሙም ገልጿል።
ለቀናት የዘለቀው ከባድ ዝናብን ተከትሎ በአካባቢው የተከሰተው ጎርፍ፤ የመሬት መንሸራተት አደጋ የዜጎቻችንን ህይወት ቀጥፏል፣ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ነው ያለው ጽህፈት ቤቱ በመልዕክቱ።
ከመጠን በላይ የሞላው የኩልፎ ወንዝም መንደሮችን፣ ቤቶችን፣ የእርሻ ስፍራዎችን፣ የአካባቢ መሠረተ ልማትን ማውደሙን አስታውቋል።
ማኅበረሰቡ በከባድ ሀዘን በሚገኝበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የነፍስ አድን ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን መቆም ይገባናል ሲልም ጥሪ አቅርቧል።