የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አርባ ምንጭ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማሃዲ፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የማገዝና የመደገፍ ስራ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር)፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ከህዝቡ ጎን በመሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ተቋማትና ግለሰቦች የላቀ ምስጋና አለን ብለዋል።