ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዱባይ ገዢ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ግርማዊ ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዱባይ ገዢ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ግርማዊ ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያይተዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት የዱባይ ገዢ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ግርማዊ ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱምን አግኝቼ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በሁለቱ ሀገሮቻችን እና ሕዝቦቻችን መካከል ስላለው ጠንካራ የቢዝነስ፣ ትምህርት እና ባህል ትስስር ተነጋግረናል ሲሉም ገልጸዋል።


 

ከዚህች ጠንካራ፣ ውብ እና ጽኑ ከተማ ጋር ያለን ትስስር በቀጣይ ጉብኝቶችም ይጠናከራል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም