ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2018(ኢዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የጸና ወዳጅነት፣ በመተማመን ላይ የተመሠረተ ትብብር! ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፡፡
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በነበረኝ የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተገናኝቼ ተወያይተናልም ብለዋል።
ውይይታችን በኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉም ተናግረዋል።
ለተደረገልኝ አቀባበል እና በሀገሮቻችን መካከል የፀና ወዳጅነታችንን የበለጠ ለማጠናከር ለተጋራነው የፀና አቋም ምስጋናዬ የላቀ ነውም ብለዋል።