እስካሁን ከ9 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ኢዜአ አማርኛ
እስካሁን ከ9 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ9 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበው የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ የቅድመ-ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል።
ቦርዱ የመራጮች ምዝገባን በተመለከተና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 መጀመሩን አስታውሰዋል።
በዚህም የመራጮች ምዝገባ በዲጂታል እና በማኑዋል እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ወደ ተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መሰራጨቱን ገልጸው፤ እስካሁን ከ9 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበው የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።