ቀጥታ፡

ሸገር ከተማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2018 (ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ ተጀምሯል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሸገር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

አሚር አብዶ እና ሚሊዮን ኃይሉ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ሸገር ከተማ በ30 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በ29 ነጥብ ከነበረበት 9ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ዝቅ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና መቻል ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ፋሲል ከነማ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ከድል ርቋል።

መቻል በ36 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከምድረ ገነት ሽሬ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህር ዳር ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም