ቀጥታ፡

ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ መጋቢት 13 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2018 (ኢዜአ)፦ 23ኛው ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ።

የውድድሩ አዘጋጅ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫውን አስመልክቶ ዛሬ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። 


 

በዝግጅቱ ላይ የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር፤ ሴቶች በዓላማ ጠንክረው ከሠሩ ያሰቡበት ደረጃ መድረስ ይችላሉ፤ እናንተ ለሀገር ተስፋዎች ናችሁና በርቱ ብላለች።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አሰግደው ኃይለ ጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ በእቴጌ መነን ወ ጎበዝ፣ አስተዋይ እና የወደፊቷ ኢትዮጵያ መሪ የሆኑ ሴቶች እየተማሩበት ነው ብለዋል።


 

መጋቢት 13 የሚኖረው ሩጫ ከምንም በላይ አብሮነታችንን የምናሳይበት እንዲሆን አብረን እንሠራለንም ነው ያሉት።

መነሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በማድረግ በሚካሄደው ውድድር፤ 16 ሺህ ሴቶች፣ ከ150 በላይ አትሌቶች እና 25 ተምሳሌት ተብለው የተሰየሙ ሴቶች ይሳተፋሉ። 

ሩጫው "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚካሄድ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም