ቀጥታ፡

ባየር ሌቨርኩሰን እና አርሰናል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ  መርሐ-ግብር ባየር ሌቨርኩሰን እና አርሰናል ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።


በቤይ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሮበርት አንድሪች በ46ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሌቨርኩሰን መሪ ሆኗል።

ካይ ሃቫርትዝ በ89ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያሳረፈው ጎል አርሰናልን አቻ አድርጓል።

ሃቫርትዝ በልጅነት ክለቡ ላይ ግብ አስቆጥሯል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም