በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ወደ ድል መንገድ ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ወደ ድል መንገድ ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት አዳማ ከተማ ይርጋጨፌ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምስር ኢብራሂም በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
ግቡን ያስቆጠረችው ምስር ኢብራሂም የጨዋታው ኮከብ በመሆን ተመርጣለች።
ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አዳማ ከተማ በ20 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አምስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በ11 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች ድል አላስመዘገበም።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ18ኛ ሳምንት ጨዋታ ሸገር ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 0 አሸንፏል።