በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ሸገር ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዓይናዓለም አለማየሁ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። ማርታ ወልዴ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ሀትሪክ የሰራችው ዓይናዓለም አለማየሁ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ሸገር ከተማ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያስመዘገባቸውን ድሎች ብዛት 12 አድርሷል።
በውድድር ዓመቱ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።