ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህም መሠረት፦

- ሌ/ጄኔራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

- ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

- አቶ ኤርዚቅ ኢሳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም