ጋላታሳራይ ሊቨርፑልን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ጋላታሳራይ ሊቨርፑልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ መርሐ-ግብር
ጋላታሳራይ ሊቨርፑልን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በራምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማሪዮ ሌሚና በሰባተኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጅል ቫንዳይክ በ70ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ጥፋት በመሰራቱ ምክንያት ተሽሯል።
በጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር የታየ ሲሆን፤ ሊቨርፑል ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች በማድረግ የተሻለ ነበር።
የጋላታሳራይ የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ሊቨርፑልን ፈትኖታል።
የባለሜዳው ጋላታሳራይ ደጋፊዎች ድጋፍ አሰጣጥ ለጨዋታው ተጨማሪ ድምቀት ሰጥቶታል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ይካሄዳል።
ቡድኖቹ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሊግ እርከን (League Phase) ተገናኝተው ጋላታሳራይ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።