ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እፀገት ግርማ እና እሙሽ ዳንኤል የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ፅግነሽ አዴ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እፀገነት ግርማ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።


 

በሊጉ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ47 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተረክቧል።

በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ30 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም