ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር በመጋቢት ወር ታደርጋለች

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የሚያደርጋቸው የማጣሪያ  ጨዋታዎች ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት ይፋ ሆኗል።

በዚህም መሠረት የመጀመሪያው ጨዋታ ሳኦቶሜ የሜዳ ጨዋታዋን ለማድረግ በመረጠችው ሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በድሬዳዋ ስታዲየም መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከናወን አመልክቷል።

36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኬንያ፣ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት እ.አ.አ ጁን 2027 ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም