በሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ አትላንታ ከባየር ሙኒክ ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ - ኢዜአ አማርኛ
በሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ አትላንታ ከባየር ሙኒክ ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል።
በዕለቱ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ምሽት 5 ሠዓት ላይ አትላንታ ከባየር ሙኒክ በቤርጋሞ ስታዲየም ይጫወታሉ።
አትላንታ በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን በደርሶ መልስ 4 ለ 3 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።
ባየር ሙኒክ በሊግ እርከን ምዕራፍ በ21 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በቀጥታ ጥሎ ማለፍ ገብቷል።
እ.አ.አ የ2024 የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አትላንታ እና የሦስት ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊጉ አሸናፊ ባየር ሙኒክ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና ምሽት 5 ሠዓት ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኒውካስትል በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የአዘርባጃኑን ካራባግን በደርሶ መልስ 9 ለ 3 በመርታት ጥሎ ማለፍ ገብቷል።
ተጋጣሚው ባርሴሎና በ16 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በቀጥታ ጥሎ ማለፍ መግባቱ ይታወቃል።
በራምስ ፓርክ ስታዲየም ጋላታሳራይ ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ በራምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።
የቱርክዬው ጋላታሳራይ በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ጁቬንቱስን በድምር ውጤት 7 ለ 5 በማሸነፍ ጥሎ ማለፍ መግባቱ ይታወቃል።
ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ በቀጥታ 16 ውስጥ ገብቷል።
ክለቦቹ በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ተገናኝተው ጋላታሳራይ 1 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።
በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም አትሌቲኮ ማድሪድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር ምሽት 5 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
አትሌቲኮ ማድሪድ በጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የቤልጂየሙን ክለብ ብሩዥ በደርሶ መልስ 7 ለ 4 አሸንፏል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ17 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዞ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብቷል።
የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳሉ።