ቀጥታ፡

ዌስትሃም ዩናይትድ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የመጨረሻ የጥሎ ማለፍ መርሐ-ግብር   ዌስትሃም ዩናይትድ ብሬንትፎርድን በመለያ ምት አሸንፏል ።

በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጃሮድ ቦውን በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ለዌስትሃም ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኢጎር ቲያጎ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ለብሬንትፎርድ ግቦቹን አስቆጥሯል።



 

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በመጠናቀቁ 30 ደቂቃ ተጨምሯል።

በጭማሪ ሰዓትም ግብ ባለመቆጠሩ ምክንያት አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ማምራት ግድ ሆኗል።

በዚህም ዌስትሃም 5 ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ ያለፈ የመጨረሻው ቡድን ሆኗል።

በሩብ ፍጻሜው ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል።



 

በወጣው የሩብ ፍጻሜ ድልድል ሳውዝሃምፕተን ከአርሰናል ፣ ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል፣ቼልሲ ከፖርት ቬል እና ዌስትሃም ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታሉ።

የኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መጋቢት 26 እና 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም