የኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማምሻውን በዌስትሃም ዩናይትድ ለንደን ስታዲየም ተካሂዷል።
በዚሁ መሰረት ሳውዝሃምፕተን ከአርሰናል ፣ ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል፣ ቼልሲ ከፖርት ቬል እና የዌስትሃም ዩናይትድና ብሬንትፎርድ አሸናፊ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታሉ።
ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መጋቢት 26 እና 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
የኤፍኤ ካፕ የጥሎ ማለፍ የመጨረሻ መርሐ-ግብር ዛሬ በዌስትሃም ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ መካከል ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በለንደን ስታዲየም ይካሄዳል።