ቀጥታ፡

የገጠር ኮሪደር ሥራው በአካባቢው በተገኙ ቁሳቁሶች፤ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወነ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን ነው

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራው የገጠር ኮሪደር ሥራ በአካባቢው በተገኙ ቁሳቁሶች፤ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወነ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ተናገሩ ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)‎ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሃረሪ ክልል የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል ፡፡


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ እቅድ እና ተግባራዊ የአሰራር ውጤት ያሳየ ነው ብለዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም