ቀጥታ፡

በተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በጣልያን ሴሪ አ የ28ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ- ግብር ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን 1 ለ 0 አሸንፏል።


 

በሳን ሲሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የክንፍ ተጫዋቹ ፔርቪስ እስቱፒናን በ35ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

በጨዋታው ኢንተር ሚላን በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ክለቦቹ ግልጽ የግብ እድሎችን በመፍጠር ተመጣጣኝ ነበሩ።

246ኛው የሚላን ደርቢ በኢንተር ሚላን አሸናፊነት ተጠናቋል።

በሊጉ 17ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኤሲ ሚላን በ60 ነጥብ ሁለተኛ ይዟል።



ከሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ዝቅ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢንተር ሚላን በ67 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።

ሁለቱ ክለቦች ዋንጫውን ለማንሳት እየተፎካከሩ ይገኛል።

ቡድኖቹ በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኤሲ ሚላን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም