ሊድስ ዩናይትድ ሳውዝሃምፕተን እና ፖርት ቫሌ ለኤፍኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ አለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ሊድስ ዩናይትድ ሳውዝሃምፕተን እና ፖርት ቫሌ ለኤፍኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የጥሎ ማለፍ መርሐ-ግብር ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ኖርዊች ሲቲን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ሲን ሎንግስታፍ፣ ጋብርኤል ጉድሙንሰን እና ጆኤል ፒሮ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ሳውዝሃምፕተን ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ሮስ ስቲዋርት በ90ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በእንግሊዝ ሶስተኛ የሊግ እርከን (ሊግ ዋን) የሚገኘው ፖርት ቫሌ ባልተጠበቀ ሁኔታ ሰንደርላንድን 1 ለ 0 ረቷል።
በቫሌ ፓርክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቤን ዋይን በ28ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቶቹን ተከትሎ ሊድስ ዩናይትድ፣ ሳውዝሃምፕተን እና ፖርት ቫሌ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
አጠቃላይ ሩብ ፍጻሜ የገቡ ክለቦች ብዛት ሰባት ደርሷል።
አርሰናል፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ሌሎች ሩብ ፍጻሜ የገቡ ክለቦች ናቸው።
የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የመጨረሻ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ነገ በዌስትሃም ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ መካከል ይደረጋል።