ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በወላይታ ድቻ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሲዳማ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ኪዳኔ አሰፋ፣ መልካሙ ቦጋለ እና ያሬድ ዳርዛ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አዲሱ ፈራሚ አቤል ያለው የሲዳማ ቡናን ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በ42 ነጥብ ላይ ረግቷል።

በውድድሩ ዓመቱ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ በ26 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።

 

በሌላኛው መርሐ-ግብር መቻል እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው የተደረገው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ነው።

ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ35 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ሲይዝ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ25 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

 

ሸገር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢኒያም ፍቅሩ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ሸገር ከተማ በ27 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ25 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 ረቷል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናትናኤል ዱባለ እና ሩዋንዳዊው ፓትሪክ ሲቦማና የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሀምዛ ሱልጣን ለኢትዮጵያ ቡና ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ34 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በ29 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም