በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር መቻል ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቱሪስት ለማ በዘጠነኛው ደቂቃ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
የመቻሏ ነጻነት ፀጋዬ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ35 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ለስምንተኛ ጊዜ የተሸነፈው ሲዳማ ቡና በ21 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ተከትሎ 17ኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የ18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከመጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።