የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር በሲዳማ ቡና እና መቻል መካከል ዛሬ ይደረጋል።
ጨዋታው ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።
ሲዳማ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በስድስቱ ድል ሲቀናው በሰባቱ ተሸንፏል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 16 ግቦችን ሲያስቆጥር 22 ጎሎችን አስተናግዷል።
ቡድኑ በ21 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው መቻል በበኩሉ በ16 ጨዋታዎች በዘጠኙ ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ አምስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። 26 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 10 ጎሎች ተቆጥረውበታል።
መቻል በ32 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በ16ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። መቻል ከሸገር ከተማ ሁለት አቻ ተለያይቷል።
ሲዳማ ቡና ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ፣ መቻል ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር በአራተኛ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው።
በወቅቱ ቱሪስት ለማ ሁለቱን ግቦች ለመቻል አስቆጥራለች። ምትኬ ብርሃኑ የሲዳማ ቡናን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፋለች።