ማንችስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ጥሎ ማለፍ መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦማር ማርሙሽ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሳቪኒሆ ቀሪዋን ጎል ለውሃ ሰማያዊዎቹ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሃርቪ ባርንስ ለኒውካስትል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።
ውጤቱን ተከትሎ የሰባት ጊዜ የኤፍኤ ካፕ አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
በአንጻሩ የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ኒውካስትል ዩናይትድ ከኤፍኤ ካፕ ተሰናብቷል።
ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ በሁሉም ውድድሮች አምስት ጊዜ ተገናኝተው ሲቲ አራት ጊዜ ሲያሸንፍ ኒውካስትል በቀሪው ጨዋታ ድል ቀንቶታል።