ቀጥታ፡

“ነጃሺ ለሀገር” 6ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2018(ኢዜአ)፦ 6ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት “ነጃሺ ለሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በኢፍጣር መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ዑስታዞች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣በዚሁ ጊዜ ለመገናኛ ብዙሃን፤ የረመዳን ወር የመሰባሰቢያና የአብሮነት ወር መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም የረመዳን ወር አንድነት የሚንጸባረቅበት፣ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበትና አብሮነት ይበልጥ የሚጠናከርበት የመተሳሰብ ወር ነው ብለዋል።

ሰድስተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብርም አንድነትና አብሮነት ማጠናከሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም