በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አርባምንጭ ከተማ እና አዳማ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው የተካሄደው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው።
ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። አዳማ ከተማ በ17 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።