ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።



አዲስ አበባ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በሁለቱ አሸንፎ በስድስቱ በ12 ተሸንፎ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ ስምንት ግቦችን ሲያስቆጥር 32 ጎሎችን አስተናግዷል።

ቡድኑ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ሃዋሳ ከተማ በበኩሉ በ16 ጨዋታዎች ዘጠኝ ጊዜ ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ አምስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። 28 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 11 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

ሃዋሳ ከተማ  በ32 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይጫወታሉ።



በሌላኛው መርሐ-ግብር ባህርዳር ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ባህርዳር ከተማ ከሸገር ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ባህር ዳር ከተማ በሊጉ 16 ጨዋታዎች አድርጎ ሶስት ጊዜ ድል ሲቀናው በ12ቱ ተሸንፏል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይቷል። ስምንት ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 22 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

ቡድኑ በ10 ነጥብ 12ተኛ ደረጃን ይዟል።

በውድድር ዓመቱ ካከናወናቸው 16 ጨዋታዎች መካከል 10ሩን ያሸነፈው ሸገር ከተማ በአምስቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ አንድ ጨዋታ ነጥብ ጥሏል።

በ16ቱ ጨዋታዎች 26 ግቦችን ሲያስቆጥር 18 ጎሎችን አስተናግዷል። ሸገር ከተማ በ31 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ጨዋታው ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።



አርባምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በሊጉ ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ያሸነፈው አርባምንጭ ከተማ በዘጠኝ ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

አዳማ ከተማ በ16 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ16ኛ ሳምንት አርባምንጭ ከተማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዳማ ከተማ በሲዳማ ቡና ሽንፈት አስተናግደዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ከሽንፈቱ አገግመው ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም