ቀጥታ፡

ሊቨርፑል በኤፍኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ የገባ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የአምስተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ሊቨርፑል ዎልቭስን 3 ለ 1 አሸንፏል።



በሞልኒው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንዲ ሮበርትሰን፣ መሐመድ ሳላህ እና ከርቲስ ጆንስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሂ-ቻን ዋንግ ለዎልቭስ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው ላይ ሊቨርፑል ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ የመጀመሪያ ክለብ ሆኗል።

 

የዎልቭስ የኤፍኤ ካፕ ጉዞ አምስተኛ ዙር ላይ ተገቷል።

ሁለቱ ቡድኖች ከቀናት በፊት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ተገናኝተው ዎልቭስ 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር እስከ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም