ቀጥታ፡

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይርጋጨፌ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እፀገነት ግርማ፣ እሙሽ ዳንኤል እና ረድኤት አስረሳኸኝ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

አዳነች አስፋው ለይርጋጨፌ ቡና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ትዕግሥት አዳነ የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጣለች።

በሊጉ 14ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ44 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ንግድ ባንክ ከመሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ ተደርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ  ቡና በ11 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ብዛት ወደ 13 ከፍ በማድረግ በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክሩ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ዳግማዊት ሰለሞን  (19 ግቦች) በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። 

ዛሬ በተደረጉ የ17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ልደታ ክፍለ ከተማ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም