ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27 /2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዙፋን ደፈርሻ፣ ማህሌት ምትኩ እና ዳግማዊት ሰለሞን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዝናሽ ሰለሞን ለድሬዳዋ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

የኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫዋቿ ዙፋን ደፈርሻ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥቡን ወደ 46 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል።

በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ19 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫዋቿ ዳግማዊት ሰለሞን በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ጎሎች ብዛት 
ወደ 19 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቷን አጠናክራለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም