ቀጥታ፡

በመዲናዋ ለሚከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27 /2018(ኢዜአ)፦ ነገ በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ነገ ከቀኑ 5 ሠዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የኢፍጣር ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ፦

👉ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን

👉 ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ

👉ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል

👉 ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ

👉 ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ

👉ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ

👉ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ያመለከተው ፖሊስ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም